Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት
  • Address ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መውጫ መንገድ ካቶሊክ ት/ቤት ጎን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912818102
  • Website
  • Deadline27 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-03-27 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Agricultural

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በክልሉ ከሚገኙ መስኖ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሁለት አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶችን የጥናትና ዲዛይን ሥራ ለማሠራት በዘርፉ ልምድ ያላቸውን አማካሪ /ፍሪላንሰር/ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 0002/2018

 

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በክልሉ ከሚገኙ መስኖ ፕሮጀክቶች ውስጥ ሁለት አነስተኛ መስኖ ፕሮጀክቶችን የጥናትና ዲዛይን ሥራ ለማሠራት በዘርፉ ልምድ ያላቸውን አማካሪ /ፍሪላንሰር/ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-

1.     የታደሰ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ

3.     ተጫራቾች በጨረታ TOR ላይ የተዘረዘረውን መስፈርት አሟልታችሁ ኒካል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ቴክኒካል ኮፒ ሁለት ፋይናንሻል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ፋይናሽያል ኮፒ ሁለት ለየብቻ በማድረግ በፖስታ አሽጋችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 830 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ከፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከቀነ 830 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 900 ሰዓት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።

4.     ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር TOR ሰነድ በነፃ ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ክፍል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.     ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912818102/0911995805 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የድርጅቱ አድራሻ ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መውጫ መንገድ ካቶሊክ /ቤት ጎን ላይ ነው፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት

Save Tender