የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
የጨረታ መነሻ ነጠላ ዋጋ በቁጥር |
የጨረታ ጠቅላላ ዋጋ
|
የጨረታ መ.ቁጥር
|
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀት |
40,000 (በቁጥር)
|
9.00 (ዘጠኝ ብር)
|
360,000.00 (ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ)
|
አ/አ/ከ/መ/ባ/ን/ማ/01/2018
|
30 ቀን
|
መጋት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00
|
መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:30
|
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባለስልጣን መ/ቤቱ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር135 በመምጣት ብር 200 በመግዛት በገርጂ ቱቦ ማምረቻ በሚገኘው የባለስልጣን መ/ቤቱ ፕ/ፅ/ቤት በመሄድ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
1. የተጠቀሰውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ቀን ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ሳር ቤት በሚገኘው በባለስልጣን መ/ቤቱ 3ኛ ፎቅ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 144 ለዚሁ ጉዳይበተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾቹ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያስረዳ ህጋዊ ሰነድ የነዋሪነት መታወቂያ ፓስፖርት ወይም ፋይዳ ምዝገባ ማያያዝ አለባቸው፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መከፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 144 ይከፈታል።
5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድር ራሳቸውን የሚያገሉ ወይም ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀባቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡
7. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ስልክ ቁጥር 011-3-72-89-47
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
