የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ቢሮ እና ለሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም በሎት አንድ 1 የደህንነት ካሜራ ዕቃ አቅርቦት ግዥና የደህንነት ካሜራ ዝርጋታ ስራዎች፣ በሎት ሁለት 2 የኔትወርክ ዕቃ አቅርቦት ግዥና የኔትወርክ ዝርጋታ ስራዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና የዝርጋታ ስራዎች ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ ቢሮ እና ለሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም በሎት አንድ 1 የደህንነት ካሜራ ዕቃ አቅርቦት ግዥና የደህንነት ካሜራ ዝርጋታ ስራዎች፣ በሎት ሁለት 2 የኔትወርክ ዕቃ አቅርቦት ግዥና የኔትወርክ ዝርጋታ ስራዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና የዝርጋታ ስራዎች ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡ የግዥ ጨረታ ቁጥር 05
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት መስክ በሎት እና በሎት 2 በተገለፀው በዘርፉ ብቻ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው /TIN NUMBER/ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመገቡ፤ ከመንግስት ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ
2. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠየቀውን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ ከሚያቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond Guarantee security/ ብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank Guarantee ወይም የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ /CPO/ በማያያዝ ከቴክኒካል የመጫረቻ ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም።
4. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ከሞሉ በኋላ የጨረታውን ሠነድ ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ ፋይናንሽያል አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንደገና በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው በኤንቨሎፑ ላይ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም አርፎበት በሰም ታሽጎና ተፈርሞ ፖስታው እስከ አስራ አንደኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ወደ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. የሂሣብ ስህተት (Arithmetic Error) ማስተካከያ አርትሜቲክ ቼክ ሲደረግ የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላለ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
6. ኮሚሽኑ በቅድሚያ የቴክኒካል ሰነድ ልየታ በማድረግ ለተጫራቾች ውጤቱን በመለጠፍ የሚያሳውቅ እና የቅሬታ ጊዜ በመስጠት ብቁ የሆኑትን ተጫራቾች በመለየት ወደ ፋይናንሻል ምልከታ የሚሄድ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች ስራው በሚሰራበት ቦታ በአካል በመገኘት የሳይት ጥናት ማድርግ አለባቸው ለዚህም የሳይት ጥናት ማረጋገጫ ከስፍራው በመውሰድ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ሰነዱን ከሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግዢ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአስር/ የስራ ቀናት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
9. በዚሁ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በኮሚሽኑ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳሬክቶሬት ይከፈታል፡፡
10. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታው ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል የማይፈጽም ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦና የBank Guarantee ይወረስባቸዋል፡፡
12. የሚቀርበው የዕቃና የዝርጋታ አገልግሎት ግዥ ብዛት ሁኔታ በሚሸጠው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መመሪያውን በሚገባ በማንበብ መወዳደር ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ማብራሪያ የያዘ ስለሆነ ይበልጥ ተቀባይነት አለው።
13. ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-2127875 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
