ለሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ቀለብ እህል ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጥ እና ለሲቪል ሠራተኞች ደንብ ልብስ ከሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም ለ120 ቀናት ከሚያቀርቡ ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማኅበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ለሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የሕግ ታራሚዎች ቀለብ እህል ጥራጥሬና ሸቀጣሸቀጥ እና ለሲቪል ሠራተኞች ደንብ ልብስ ከሚያዚያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም ለ120 ቀናት ከሚያቀርቡ ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ማኅበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-
1ኛ. በየዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2ኛ. የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3ኛ የጨረታው ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ማስከበሪያ ለእህልና ጥራጥሬ ብር 50000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሸቀጣ ሸቀጥና ደንብ ልብስ ብር 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ በጥሬ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችል፤
4ኛ. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ያለውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የመንግሥት የሥራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5ኛ. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
6ኛ. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
7ኛ. የጨረታው አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጪ ለማሻ ማ/ተቋም ማስረከብ የሚችል
8ኛ. ተጫራቾች አሁን ባቀረቡት ዋጋ ለ4 ተከታታይ ወር ማቅረብ የሚችል ሲሆን፤ በመሐሉ የድርድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
9ኛ. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ
10ኛ. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቀም
