አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ባለ 10 ወለል (G +10) ዘመና ህንጻ በሙሉ ወይም በከፊል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 005/2018
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ባለ 10 ወለል (G +10) ዘመና ህንጻ በሙሉ ወይም በከፊል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-06 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ትችላላችሁ።
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3. አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ማስፈርና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማና ማህተም በመምታት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ጠቅላላ የኪራይ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከመወዳደሪያ ፖስታጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው በ11ኛው ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከሰዓት በኋላ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
9. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ፍላሚንጎ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-06 ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 11 92 45 97
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
