በደቡብ ወሎ ዞን የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል solar Security (CCTV camera}፣ የአይን ምርመራ የህክምና መሣሪያ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል solar Security (CCTV camera}፣ የአይን ምርመራ የህክምና መሣሪያ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል
1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት/
2. የዘመኑን ግብር የከፈለ /ለች
3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ /ነች
4. ጨረታው የሚከናወነው በሎት ነው
· ሎት 1. solar 20kw solapanel with inverter
· ሎት 2. Security (CCTV) camera
· ሎት 3 የአይን ምርመራ የህክምና መሣሪያዎች
· ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከሆስፒታሉ ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ድምር ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል 16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር 0914344306/0934370254 /0923747044 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የመካነሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል
