በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በቦንጋ ቅርንጫፍ ተከማችቶ የሚገኘውን ሩዝ የምግብ እህል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ የሩዝ የምግብ እህል ሽያጭ ጨረታ የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ የግ/ው/ሽ/ሜ/አ/ዘ/ግጨ/ሸ05/2018 በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ በቦንጋ ቅርንጫፍ ተከማችቶ የሚገኘውን ሩዝ የምግብ እህል ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሱ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ንገድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርነት ወረቀት፤ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክርነት ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችል እና በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት በመንግስት ግዥ አቅርቦት የተመዘገበ መሆን ኣለበት፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በባንክ የተመሰከረ CPO በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ ስም ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለ30 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ የሩዝ የምግብ እህል ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨመራል።
4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ሐሙስ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እንዲሁም ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-5:30 ከሰዓት በኋላ ከ7:30- 10:30 በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት በኢግሥኮ የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 እንዲሁም በቦንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው ሚያዝያ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሚያዝያ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 እና በቦንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ዝርዝር መሰረት መጫረት ይቻላል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፤
8. ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
አዲስ አበባ 0114-70-84-75/0116-66-23-90
አዳማ 0221 11-21-22/0221-11-31-56
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
የግብርና ውጤቶች ሽያጭና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ዘርፍ
