Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline30 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-04-30 00:00:00
  • Categories Research Consultant , Study And Research And Tools

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ 5 የክልል ኤርፖርቶች ውስጥ የዱር እንስሳት አደጋ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና ጥናት (ECOLOGICAL INVESTIGATION AND ANALYSIS OF WILDLIFE HAZARD AT ETHIOPIAN AIRPORTS) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ -SSNT-T 611

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 5 የክልል ኤርፖርቶች ውስጥ የዱር እንስሳት አደጋ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና ጥናት (ECOLOGICAL INVESTIGATION AND ANALYSIS OF WILDLIFE HAZARD AT ETHIOPIAN AIRPORTS) በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ ሥነ-ምህዳራዊ ምርመራ እና ትንተና አጥኚዎችና አማካሪዎችን ስራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1.     ተጫራቾች በአገር ውስጥ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ተመዝግበው የምርመራ እና ትንተና አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው እና በዘርፉ ለመስራት 2018 . ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2.     የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3.     በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T 611 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።

5.     በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አንድ መቶ ሰባ ሺህ ብር (170,000.00 ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ .. (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

6.     አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።

-       ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሀሙስ ሚያዝያ 22,208 . ከቀኑ 830 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028

-ሜይል: AddisGEW@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 

Save Tender