Tender Detail

Tender Details

  • Company Development Bank of Ethiopia
  • Address , Phone: 251115506020
  • Website
  • Deadline26 May 2026, 3:43 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-04-26 15:43:00
  • Categories Office Equipment

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


የጨረታማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለብድር ገንዘብ ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የመያዣ ንብረቶች በልዩ ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁ
የተበዳሪው/     የመያዣ ሰጪው ስም
የንብረትአድራሻ
የንብረት ዝርዝር
የቦታ ስፋት (በሄክታር)
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)
የጨረታሁኔታ
የጨረታ ደረጃ
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ ክ/ከተማ  ወረዳ 08
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤ የህንፃ ግንባታዎች፣የኤልክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት
1,678 ከሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
ልዩ ድርድር
አንደኛ
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም               ከጠዋት 4፡00-6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ፤

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ሆኖ ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ በማስገባት ከ4፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ባንኩ ያስያዘውን ገንዘብ ይወርሳል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
  6. አንዳንድ የድርጅቶች ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ፤ታክስ ለመክፈል ይገደዳል፡፡
  7. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  8. ባንኩ ንብረቱን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል፡፡
  9. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ያሳወቃል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ የማስፈፀም ሃላፊነት አለበት፡፡
  10. በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፡፡
  11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011–524-53-73/011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

Save Tender