በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በ2008 በጀት ዓመት ሎት 1 የመምህራን ቅጥር፣ ዝውውር፣ የሙያ ብቃት ምዘና አላይን ምዝገባ Softwire እና ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 16/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በ2008 በጀት ዓመት ሎት 1 የመምህራን ቅጥር፣ ዝውውር፣ የሙያ ብቃት ምዘና አላይን ምዝገባ Softwire እና ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡- ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡
1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወርቀት ያላቸው፣
2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 - 6:00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ60 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንክ ጋራንቲ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ ቴክኒካልና ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በአንድ ፖስታ በማድረግ ከአንድ ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው፤
7. የጨረታ ግምገማን በሚመለከት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አብሮ የሚከፍት ይሆናል፡፡
8. ጨረታው ለ2 ወራት /60 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
9. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ማግኘት ይቻላል፡፡
10. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-221-70-02
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
