Tender Detail

Tender Details

  • Company በማ/ኢ/ክ/ል/ ስልጢ ዞን ፋ/መምሪያ ወራቤ
  • Address , Phone: 0467710586
  • Website
  • Deadline08 Jun 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-06-08 02:38:00
  • Categories Maintenance And Repair , Vehicle (Garage Service)

የስልጤ ዞን ፋ/መምሪያ የዞኑን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የስልጤ ዞን ፋ/መምሪያ የዞኑን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

v  በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው

v  የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል

v  በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርቲፊኬት

v  የአመቱ በመንገድም ይሁን ግቢ ውስጥ ለሚደርስ አደጋ (ለህይወት እና ንብረት) የታደሰ የሙሉ ኢንሹራንስ ውል ማቅረብ የሚችል፤

v  ተጫራቹ ከሚመለከተው አካል አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል

v  የጋራጅ ቤቱ ስፋት ከ2000 ካሬ ያለነሰ ሆኖ የግል ከሆነ የካርታ ኮፒ የኪራይ ከሆነ የአንድ አመት የኪራይ ውል ማቅረብ የሚችል

v  በአዲሱ የፌደራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የደረጃ አሰጣጥ መሰረት ደረጃ አራት ወይም ከዚያ በላይ ያለው ሆኖ ለደረጃ የተሰጠውን ቴክኒካል መስፈርት ሟሟላት የሚችል።

v  ለደረጃው የሚያስፈልጉትን ሰራተኞች ለሶስት ወር በተከታታይ ደምወዝ የተከፈለበትን ፔሮል፣ የኮንትራት ሰራተኞች ካሉ ውል እንዲሁም በመስፈርቱ መሰረት የሁሉንም የትምህርት ዶክመንት ማያያዝ የሚችል እና የሰራተኞችን የስራ ግብር ለገቢ ሰብሳቢ መ/ ቤት የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

v  የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የ100,000 (መቶ ሺ ብር) ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ጋራንት ማያያዝ የሚችል

v  ተጫራቾች ሰነዱን ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ 1000 ብር በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመሙላት ፋይል እና ቴክኒካል ሰነዱን አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚያው ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

v  የጨረታ ሳጥኑ በ20ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 2ኛው ቀን የስራ ቀን ከልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ 046 771 0586 መደወል ይችላሉ

 

በማ/ኢ/ክ/ል/ ስልጢ ዞን ፋ/መምሪያ ወራቤ

 

Save Tender