በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ባለ18 ባትራ የዳቦ ቤት መጋገሪያ ከነሙሉ እቃው፣ ከመጋገሪያ እና መሸጫ ሱቁ ብቃትና ፈቃድ ያላቸውን አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ስር የሚገኘው የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ባለ18 ባትራ የዳቦ ቤት መጋገሪያ ከነሙሉ እቃው፣ ከመጋገሪያ እና መሸጫ ሱቁ ብቃትና ፈቃድ ያላቸውን አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. የመስሪያ ካፒታል 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር እና በላይ የባንክ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከማዕከሉ አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በማዕከሉ አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በአስረኛው የስራ ቀን 8:00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልፅ ይከፈታል።
9. የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።
10. የጨረታ አሸናፊው በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጽሁፍ በተገለጸ በ7(ሰባት) ቀናት በኋላ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በመያዝ ወዲያውኑ ወደሥራ ክፍሉ መጥቶ ውል መፈጸም አለበት ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ: -
ተጫራቾች መጋገሪያ ማሸኑንና የመሸጫ ሱቁን በማዕከሉ በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አጠገብ ወይንም ከመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከሚገኘው አደባባይ ወደ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት መንገድ በስተግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል
