Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ድጋሚ የወጣ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 437/18

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ኘሮግራም አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ/ቁ

 

የዕቃው አይነት

 

መለኪያ

 

ብዛት

 

የጨረታ ማስከበሪያ

 

የሚታሸግበት ሰዓት

 

ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ

 

1

 

ላፕቶፕ ኮምፒዉተር

 

በቁጥር

 

4

 

100,000

 

በ31ኛው ቀን 

በ5፡00 ታሽጎ 

በዕለቱ 5፡10 ይከፈታል

 

ደ/ኢ/ግ/ቢሮ 

ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ

 

2

 

ዴስክቶፕ ኮምፒዉተር

 

በቁጥር

 

3

 

3

 

ፕርንተር

 

በቁጥር

 

3

 

4

 

LCD

 

በቁጥር

 

2

 

5

 

የLCD Power Bank

 

በቁጥር

 

2

 

6

 

Copy Machine All in one

 

በቁጥር

 

1

 

 

በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

Ø  ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።

Ø  በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒ-ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው።

Ø  ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 30ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ወስጥ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

Ø  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና እንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ አዘጋጅቶ በማሸግና ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ ከቶ በማሸግ በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮው ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡10 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።

Ø  ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።

Ø  የጨረታው መክፈቻ ቀን ማለትም 31ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

Ø  ከአንድ በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል።

·         ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

·         ቢሮዉ ጨረታዉን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

ለበለጠ መረጃ 046-131-0134 ይጠቀሙ።

 

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ግብርና ቢሮ

Save Tender