የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለህሙማን እና ለተማሪዎች የሚውል በ2019 የበጀት ዓመት የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች፣ እንጀራ፣ የክርስቲያን እና የሙስሊም ስጋ እና የላም ወተት በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለህሙማን እና ለተማሪዎች የሚውል በ2019 የበጀት ዓመት፡-
1. የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች
2. እንጀራ
3. የክርስቲያን እና የሙስሊም ስጋ
4. የላም ወተት በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላለችሁ፡፡
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ።
- ተጫራቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው ፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይት የለውም፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ጨረታ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የክርስቲያን ስጋ የሚያቀርበው በክርስቲያን ቄራ ማሳረዱን መረጃ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት። የሙስሊም ስጋ የሚያቀርበው በሙስሊም ቄራ ማሳረዱን መረጃ ማምጣት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ጨረታው የሚከፈተው በ27/09/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- እንጀራ ጨረታው የሚከፈተው በ27/09/2018 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የክርስቲያን እና የሙስሊም ስጋ ጨረታው የሚከፈተው በ26/9/2018 ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የላም ወተት ጨረታው የሚከፈተው በ26/9/2018 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 30,000 (ሰላሳ ሺ)) ብር በ"CBE, CBO, እና በSinge" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
