Tender Detail

Tender Details

  • Company Lion Insurance Company (S.C)
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline02 Jun 2026, 3:14 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-05-27 15:14:00
  • Categories Office Equipment

ኩባንያችን አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 


ቀን፡- 19/09/2018 ዓ.ም

ጨ/ቁ 07/2018

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፁትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃው አይነት መለኪያ ብዛት
1 Desktop Computers ቁጥር 25
2 Printers (Print Only Laser Machine)  

ቁጥር

 

08

3 Cash Safe Box 100 kg ቁጥር 04

 

በመሆኑም በዘርፉ የተመዘገበ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን እና ጨረታ እንዲሳተፉ የሚገልፅ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች ዝርዝር የመጫረቻ መስፈርቱን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ፎቅ ከፋይናነስ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ድረስ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ የእያንዳንዱን እቃ ዋጋ የምታቀርቡበትን የመጫረቻ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል በማድረግ በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ዋናው መስሪያ ቤት (4ተኛፎቅ) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ጨረታው ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዛው እለት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡

ኩባንያው የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ፡፡

  አድራሻ

አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

ኃይሌ ገ/ስላሴ ጐዳና

አንበሳ ኢንሹራነንስ ህንፃ

ስልክ፡- 0116-18-70-00/011-6-62 81 35

Save Tender