የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለእርሻ አገልግሎት የሚውል 2/ ሁለት/ ትራክተሮች ባለ 120 የፈረስ ጉልበት/120HP /ሁለት/2/ ባለ6 ሳህን አግሮ ማስተር ባልዳን እና ሁለት/2/ መከስከሻ ባለ32 ሳህን ባልዳን 32 DISC ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም.
የተጫራቾች መመሪያ
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለእርሻ አገልግሎት የሚውል 2/ ሁለት/ ትራክተሮች ባለ 120 የፈረስ ጉልበት/120HP /ሁለት/2/ ባለ6 ሳህን አግሮ ማስተር ባልዳን እና ሁለት/2/ መከስከሻ ባለ32 ሳህን ባልዳን 32 DISC ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ከሆነ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ሰለማጭበርበር ሙስና ጉቦ መስጠትና መቀበል ጭምር የኢትዮጵያ ሕጎች የተደነገገውን የሚያከብሩ መሆኑን በማረጋገጥ ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ እንደሚሰረዙና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ 5% የሚወረስና በሌሎች ጨረታዎች እንዳይሳተፍ ዕገዳ የሚጣል ይሆናል።
3. ተጫራቾች የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ድረስ የመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 60 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች ታክስ ሰለመክፈላቸው የሚያረጋገጥ ማስረጃ የታክስ ከሊራንስ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 5 በመቶ / 5% /በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ በትልቁ ፖስታ ውስጥ በመክተት ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ ጨረታው ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 60 ይከፈታል። ይህን ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሐሳብ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅታቸው ማህተም ማድረግ አለባቸው።
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ሲመለስላቸው አሸናፊ የሆነ ተጫራች በአሸነፈበት ሂሳብ ጋር ይታሰብላቸዋል።
10. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
11. የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ቦታ በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 60 ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ነው።
12. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 047 551 1468 / 09 17 80 47 27/
የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
