Tender Detail

Tender Details

  • Company በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም
  • Address ጎፋ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916877379
  • Website
  • Deadline13 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2026-06-13 10:30:00
  • Categories Food And Beverage , Firewood

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ለ12 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም ከሐምሌ 1 ቀን 2018 / ጀምሮ እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2019 / ድረስ 12 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ማጣፈጫ ቅመማቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1.     በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫቲ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር መለያ /Tin/ ቁጥር ያለው፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወርቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ CPO እና በጥሬ ገንዘብ የተረጋገጠ 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ማሳያዝ ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የመጫረቻ ሠነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

4.     የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

5.     ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም አምጥተው ማስረከብ አለባቸው።

6.     የጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተገኙ ተጫራች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /CPO/ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ //አስ/ ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል።

7.     ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።

8.     የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ዕለቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግሥት ሥራ ሰዓት ይከፈታል።

9.     በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም።

10.  ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ 09 16 87 73 79 / 09 13 88 73 30/

 

በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም

Save Tender