Tender Detail

Tender Details


ግሎባል ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ ላይ የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05-2025/26

ግሎባል ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ ላይ የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የቀረቡትን መመሪያዎች በመገንዘብ በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ተ.ቁ የተሽከርካሪው ዓይነት ብዛት
1 Nissan Pick Up 4WD 4
2 Nissan Almera Automatic Transmission 4
3 Toyota RAV4 Automatic Transmission 4WD 2
4 Nissan X-trial Automatic Transition 4WD 1
5 Nissan Micra Hatch Back 2

 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 00 /ሁለት መቶ ብር/ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዘው በመቅረብ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7 ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 5፡45 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 10፡45 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 5፡45 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ መነሻ ዋጋቸው እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንኩ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም በማሰራት እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኘውን ቅጽ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎኘ እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንጻ 7 ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት ሰዓት 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊዎች ንብረቶቹን ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ባሉበት ቦታ በአካል በመገኘት በአግባቡ ተመልክተው ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ፡- ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ስልክ ቁጥር

0115581204 ወይም 0115318156 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Save Tender