በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታት በሰንጠረዥ የተገለጹትን ለምርት ግብዓት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ከታት በሰንጠረዥ የተገለጹትን ለምርት ግብዓት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
No |
Description |
Quantity |
|
1 |
PP Raffia |
33,000 |
|
2 |
Pvc Resin |
45,000 |
|
3 |
Ldpe Middum Duty |
33,000 |
|
4 |
Hdpe for pipe |
20,000 |
|
5 |
PVC Garden Hose |
20,000 |
|
6 |
Hdpe Blow Molding |
22,000 |
በመሆኑም ተጫራቾች -
1. በኢንዱሰትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው፤ በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
3. ተጫራቹ የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
4. ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሽገ ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መግለፅ ይገባል፣
5. ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል ።
6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት በዛው ዕለት ከ30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፤
7. ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
11. ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
