የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከሀምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች፣ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ባ/ዞ/ማ/ቤ /06/2018
የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከሀምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች፣ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ (ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license)፣ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርቲፊኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier list) ማቅረብ አለባቸው::
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ከባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ ሲፒኦ ብቻ እውቅና ካለው ባንክ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ኦሪጂናል ፋይናንሺያል (ዋጋ የተሞላባት) ሰነድ ፋይናንሺያል ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ሶስቱንም ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ዕለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
5. እያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት፡፡
6. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
7. በጥቃቅን እና አነስተኛ ጥቃቅን ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5 ቀን በኋላ ከ6 ኛው ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
ማረሚያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 02224400023/0932311224 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት
