1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ማሽነሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አግ/13/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጫረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ አግ/13/09/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ማሽነሪዎች የኪራይ አገልግሎት ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/አግ/13/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚፈጽመው የተለያዩ ማሽነሪዎች ኤከስካቫተር በጃክ ሃመር፣ሎደር፣ ክሬን 50 ቶን፡ክሬን 30 ቶን፣ብትን ሲሚንቶ ማጓጓዣ ኮኮት፣ሎው ቤድ ሃይ ቤድ 16 ሜ.ኪ. የሚጭን ገልባጭ መኪና፣ፎርከ ሊፍት ባለ 8 ቶን እና ባለ 5 ቶን የኪራይ አገልግሎት ግዥ ተጫራቾች የቴከኒካል ሰነዳቸውን እና የዋጋ ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ መመሪያ ቁጥር 1070/2017 በፌዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀረ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 2ኛ ቢሮ ቁጥር 209 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/(unconditional) ቢድ ቦንድ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ማቅረብ አለባቸው።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር ቢሮ 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 011-1-85536-67 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
