Tender Detail

Tender Details

  • Company Wegagen bank
  • Address P.O.Box 1018, Tel.011-5-581279/011-5-523800/011-5-582184, Phone: 011-5-581279
  • Website
  • Deadline18 Jun 2026, 9:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-06-18 12:00:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

    ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


                                                     ወጋገን ባንክ አ.ማ

                                           ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሀራጅ ማስታወቂያ

                                          ቁጥር፡ ወጋገን 029/2018

     ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረበውን የመያዣ ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም ንብረት አስያዥ አበዳሪ

ቅርንጫፍ

የተሽከርካሪ            ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የሞተር ቁጥር        ዘመን የነዳጅ

አይነት

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ቀን
ቀን ሰዓት
1

 

 

 

በንቲ መስፍን

 

ቤኪ ትሬዲንግ ኃ/የጠ/የግ/ማህበር

 

 

ውኃ ልማት

 

የጭነት ሲኖ-ትራክ ሆው

ኢት-03-18902 LZZ5BLSF4NA094016 WD615.47220807042007 2022 ናፍጣ 7,000,000.00  

ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም

 

ከጧቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ድረስ

2 ተሳቢ ኢት-03-35126 LA99FRA36N0LFY914 2022 3,000,000.00

ማሳሰቢያ  

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  3. በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በውስጥ መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
  4. የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡
  5. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
  7. ጨረታው የሚካሄደው፡ በባንኩ ዋ/መስሪያ ቤት ህንጻ 13ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
  8. ለሀራጅ ጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
  9. ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
  10. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
  11. ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ወጋገን ባንክ አ.ማ

 

Save Tender