Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት ሎት1 የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት2 የህክምና ግብአቶች እና የኦክስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል 2019 በጀት መት ለሚፈፅማቸው ግዥዎች ማለትም ሎት1 የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ፣ ሎት2 የህክምና ግብአቶች እና የኦክስጅን ስሊንደር ጭነት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሀምሌ 1 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2019 . ለሶስተኛ ወገን በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ሰርተፍኬት፣

2.     የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3.     የሚያቀርቡት የንግድ ፍቃድ ዘርፍ የቫት ተመዝጋቢነት ግዴታ ለሆነባቸው አገልግሎቶች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡

4.     የጨረታ ሰነዱን ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ፋይ/ንብ አስ//የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.     የጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ለሆስፒታሉ CPO /በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡

6.     የቅድሚያ ግብር ዊዝሆልዲንግ ክፍያ ከብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በላይ አገልግሎቶች 3% የሚቆረጥ ይሆናል፡፡

7.     ለሰራተኞች ትራንስፖርት ጨረታ ተሽከርካሪው በወንበር 24 /ሀያ አራት/ ሰው እና በላይ የመጫን አቅም ያለው፡፡ እና የተሽከርካሪው የስሪት ዘመን እንደ ኤሮፓ አቆጣጠር 2010 እና ከዚህ ወዲህ የተመረተ፡፡

8.     ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ ሙሉ ወጪዎችንና ናፍጣ በራሱ የሚሸፈን መሆኑን ታሳቢ አድርጎ ይሆናል፡፡

9.     ለሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች የስራ ጊዜው በመንግስት የስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ /ጠዋት፣ ምሳ ሰዓትና ማታ/ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ለጭነት አገልግሎት ጨረታ ደግሞ ጭነት በሚኖርበት ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡

10. የተሽከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ፣ ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት፣ የቴክኒke ምርመራ /ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት

11. ለሰራተኞች የትራንስፖርት መኪናው በህዝብ ትራንስፖርት እና ለጭነት አገልግሎት በደረቅ ጭነት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡

12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው

13. የጨረታዎቹ አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ CPO /በጥሬ ገንዘብ/ ለሆስፒታሉ እዲያሲዙ ሲጠየቁ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

14. የሁለቱም ውለታዎች እንደ አስፈላጊነቱ በሩብ አመት፣ በግማሽ አመት ወይም የአንድ በጀት አመት ውል የሚፈፀም ይሆናል፡፡

15. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ በትክል ነጣላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋውን በመሙላት ዝርዝር አባሪ ሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

16. ጨረታው ፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸግና ከጠዋቱ 430 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

17. ለሁለቱም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል።

18. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ/ ዝግ ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

19. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

20. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913869679 0925402088 ወይም 0924854239 ደውለው ይጠይቁ፡፡

 

አድራሻ፡-

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 190 ኪሎ ሜትር ደብረሲና ከተማ

 

የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender