Tender Detail

Tender Details

  • Company መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 03 በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከጠበል መድኃኒአለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0930796413
  • Website
  • Deadline25 Jun 2026, 10:30 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price400.00
  • opening date2026-06-25 11:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Wood And Wood Working

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ Avatar of lidiya Tenders Create


የጨረታ ማስታወቂያ

የሰነድ ቁጥር 125



መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ቁሳቁሶቹም:-
1.
የተለያዩ ብረታ ብረቶችና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች (ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)
2.
ከእንጨትና ከብረት የተሰሩ ወንበሮች
3.
ከብረት የተሰሩ ቋሚ የመብራት ፖል (ምሰሶዎች) (ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)
4.
ያገለገሉ ስፕሪንግ ፍራሾች ናቸው::
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተከርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው የማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ከፍል ድረስ በመምጣት ብር400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ .. ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 500 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፦

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡


መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር

Save Tender