በሎት-5 የሁርስስ እና የቤል ትራከተር ከሞተር ውጭ የሆኑ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የሞተር ከፍል መለዋወጫ
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር: ጣበስሩ/አግ/ብግጨ/02/2018/19
ጣና በስስ ስኳር ፋብሪካ
በሎት 1 የኢንከላይንድ ፍላት ቤልት ጋይድ ሮለር የኮቲንግ ስራ
በሎት-2 የተለያዩ የፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎች
በሎት-3 የተለያዩ ኤሌክትሪካል እና ኢንስትሩመንታል መለዋወጫ ዕቃዎች
በሎት 4 የወርከ ሾኘ ዕቃዎች እና
በሎት-5 የሁርስስ እና የቤል ትራከተር ከሞተር ውጭ የሆኑ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የሞተር ከፍል መለዋወጫ
በሎት6 የዋይ ቲአ እና የአግሮትሮን ትራከተር መለዋወጫ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ሕጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታከስ ከሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ/ የምስከር ወረቀት፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ለተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂቁጥር1000057735167 በመክፈልና የባንከ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ.4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስረከቢያና መከፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው። አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ።
1. ብሎክ A ቢር ቁTE B008
2. ስልክ ቁጥር 011 5-586725 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ6ዐ ቀናት ነው።
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
ጣና በስስ ስኳር ፋብሪካ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Tana Beles Sugar Factory seeks bids for six lots of spare parts, including conveyor belt rollers, electrical and instrumental items, workshop supplies, and non-motor and motor parts for Hurss and Bell tractors. Bidders must have a valid 2018 trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration certificate.
