ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 016/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ አንድ (ሎት 1) - የህትመት ውጤቶች ከቦታ ቦታ መጓጓዣ ጋሪ (ድርጅቱ ውስጥ በመገኘት የሚፈልገውን ሥራ አይቶ ዲዛይን ሠርቶ በማቅረብ የወረቀት ማጓጓዣ ጋሪዎቹን መሥራት) አገልግሎት ግዥ፣
በጨረታ ሁለት (ሎት 2) - ሙሉ በሙሉ አውቶማቲክ የሆነ (Fully Automatic all in one machine) ወይም ጥሬ ዕቃ በመጠቀም እስከ ማንጠልጠያ ገጠማ በአንድ ላይ የሚሠራ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢት (Bag) መሥሪያ ማሽን ብዛት 1. ግዥ፣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲስ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይየማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው በመግዛት ፋይናንሺያል የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ሕንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው 7/11/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30 ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
