Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ የዕቃና አገልግሎት ግዥዎችን በሎት የተለያዩ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የኮንትራት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ የዕቃና አገልግሎት ግዥዎችን ማለትም

1.     ሎት - 1 የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ

2.     ሎት - 2 የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት

3.     ሎት - 3 የተሽከርካሪ ኢንሹራንስና እንዲሁም

4.     ሎት - 4 የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የኮንትራት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

ስለሆነም -

1.     ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin /ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ;

3.     የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴትታክስ Nat/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከከ እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

5.     የግዥ ፈጻሚ /ቤቱ ከቫት ከፍያ ላይ 7.5% እና የዊዝ ሆልዲንግ 3% ከጠቅላላ ከፍያ ላይ ቀንሶ የሚያስቀር ሲሆን በተጨማሪም የግዥ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6.     ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር ብቻ / በግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በመቅረብና በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ::

7.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የተሸከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 / ሃምሣ ሺህ ብር / እና የተሸከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኞች የትራንስፖርት ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ብር5.000.00 / አምስት ሺህ ብር / በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቹ ምርጫ በሲፒኦ (CPO) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሽገው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብአሰ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 22 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 22 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በሚቆጠር 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 401 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ይከፈታል፡፡

10.                        በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች የዕቃና አገልግሎት ግዥው በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የፑል አገልግሎት ለሚያገኙት ተቋማት በኮንትራት ውል ተይዞ የሚፈጸም ግዥ በመሆኑ ተጫራቾች በደ/ብርሃን ከተማ የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቅርንጫፍ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

11.                        የጨረታ መከፈቻው ዕለት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ፡፡

12.                        /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

13.   በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር22 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 011-681-32-41 ወይም 011-681-63-96 በመደወል መጠየቅና መረጃ ማግኘት ይችላሉ ::

 

የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

/ብርሃን

Save Tender