Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች እና ተሽከሪካሪ መኪና እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግል


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 38/2018

 

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ /ቤት በቅ//ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ /ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ተሽከርካሪዎች የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች፣ አልባሳት፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች እና ተሽከሪካሪ መኪና እንዲሁም ሎሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1.     ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2.     ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 200 - 1200 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 200-600 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብርበመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3.     በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲፒኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒ  ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ //ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወክሎቻቸውባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።

5.     ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዘኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።

6.     ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 345 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃተዘግቶ 400 (አራት ሰዓትላይ ይከፈታል።

7.     ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ቢቀር የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

8.     ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት .. (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት ከተገለጸ  3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9.     አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ  5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10.ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት COP ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11./ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር - 046 444 1415 / 046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ /ቤት

Save Tender