ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ከልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በተለያዩ የሀገሪቱ ከልሎች ለሚያከናውናቸው የጤና ስራዎች የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ማቅረብ ከሚችሉ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ከሚችሉ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትጫረቱ ተጋብዛችኋል። ተጫራቾች
1. በዘርፉ የተሰማሩበት የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
2. የንግድ ምዝገባና ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ:
3. የግብር ከፋይ ምዝገባ /Tin Number/ ማቅረብ የሚችሉ እና፣
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ በመቅረብ በማይመለስ ብር 1000.00 ( አንድ ሺህ ብር ) እንዲሳተፉ ይጋብዛል። የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልከ (የተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ) 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ማስተባበሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-6 ያሉትን ካላሟሉ ከጨረታ ይሰረዛሉ።
7. ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ያዘጋጅውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ መጠቀም አለባቸው። ተጫራች የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላስቀመጠው የእቃው አይነት እና /ወይንም መስፈርት (Specification) መሆን አለበት።
8. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በአንድ ፖስታ ሌሎች የተጠየቁ የንግድ ሰነዶችን በሌላ ፖስታ አሽጎ ማስገባት አለባቸው። ፖስታዎቹም የዋጋ ማቅረቢያ እና የንግድ ሰነዶች በሚል ተጽፎባቸው ይቀርባሉ።
9. ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በትከከል መሞላት አለበት፤ አቅርቦቱ የተጨማሪ እሴት ታከስ የማይመለከተው ከሆነ በሚሰጡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ አይካተትም።
10. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከሞሉ በኋላ ጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደ ታችም ደምረው ማስቀመጥ አለባቸው፡ የድምር ስህተት ቢኖር የተሰጠው ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል።
11. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን መፈረም እና ድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
12. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ለእያንዳንዱ እቃ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።
13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ስርዝ ድልዝ ካለ በአቅራቢው መፈርም አለበት።
14. አስረኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ አልያም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ይሆናል።
15. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር የሥራ ቀናት ይቆይና በአስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት ቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ቀይ አፈር አካባቢ በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።
16. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ በሶስት የስራ ቀናቶች ማቅረብ ይኖርበታል፤ ነገር ግን ጥራቱ በድርጅቱ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፤ ይህንን ባያድርግ ግን እቃውን ማቅረብ እንዳልቻለ ይቆጠራል፣ የአስያዘው CPO ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
17. አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ከፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለበት። ይህንን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም አይነት ክፍያ መጠየቅ አይችልም። መ/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም።
18. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሰረት ተፈጻሚነት ይኖራቸዋል።
19. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ Menschen fur Menschen ስም አዘጋጅተው በፖስታ በማሸግ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
20. የጨረታው ውጤት ጨረታው ተገምግሞ እንዳለቀ በደብዳቤ ወይም በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
21. ተጫራቾች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም።
22. በጨረታው ተሳትፎ አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በከፊልም ሆነ በሙሉ ማቅረብ ካልቻለ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል::
23. ድርጀቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰርዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114 71 42 91 / on4 71 43 58 በስራ ሰዓት ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
ሰዎች ለሰዎች ድርጅት
