Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline10 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price
  • opening date2026-07-10 22:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Animals , Animal Feed And Supply

የፈረንጅ ላሞች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

በፍ/ባለመብት መንበረ ገለታ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ታደለች ታዬ (3 ሰዎች) መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 13907 በ16/5/2017 ዓ.ም በመ/ቁጥር 119483 በ14/08/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 007 ውስጥ የሚገኙ 2 የሚታለቡ እና 2 ሌሎች የደረሱ የፈረንጅ ላሞች የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ ሂሳብ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት የፍ/አ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

 

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Save Tender