Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ድሬዳዋ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 025-4-11-65-51
  • Website
  • Deadline29 Jun 2026, 4:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-06-29 10:00:00
  • Categories Promotional Items , Humanitarian Aid Supply, Relief Items

በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ በአንላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ኦንሳይን የሐራጅ ጨረታ ቁጥር AE02/2018

 

በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ //ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ በአንላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት:-

በኦላእይን ግልጽ ጨረታ ቁጥር AE004/2018 023/10/2018 P+AR ሞባይል ቀፎዎች፤ ቴሌቪዥን በኦንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1.     በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን በአንላይን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡

2.    በኦንላይን የሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው::

3.    ኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት በአንላይን ብር 100 በመግዛት ጨረታ ላይ መሳተፍ ይቻላል= የዕቃዎችን ሳንፕል በአንላይን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::

4.    ጨረታው የሚካሄደው በኦንላይን ነው::

5.    በአንላይን የሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡

6.    ነተጫራቾች በኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለእያንዳነዱ ኮዶች የተቀመጠውን ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ዋጋ 5% በ (Tele birr) Auction Ethiopia ወይንም በባንከ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

7.    ተጫራቾች በአንላይን ሐራጅ ጨረታ ኦንላይን ከሆነበት ከ17/10/2018 4:00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 22/10/2018 4:00 ሰዓት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.    በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶፍት ኮፒ የተሰራ ከሆነ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

9.    አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡

10.  ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለጹ ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒአ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

11.    የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል

 

 

 

በጉምሩከ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender