Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Pipe Factory (APF) (የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-35-98-37-29
  • Websitehttps://www.amharapipe.et/
  • Deadline07 Jul 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-07 14:30:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Raw Materials

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው ሎት 1 Black Master Batch ብዛት 33 ቶን እና ሎት 2 Yellow Master Batch ብዛት 300 ኪሎግራም በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር APF/25/2018/Local

 

የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው

ሎት 1 Black Master Batch ብዛት 33 ቶን እና

ሎት 2 Yellow Master Batch ብዛት 300 ኪሎግራም በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጥሬ እቃዎች የማቅረቢያ ቦታ ባህርዳር እስከ ፋብሪካው የመሥሪያ ቦታ ድረስ ሲሆን በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.     ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3.     በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በኢ-ሜይል አድራሻችን amharapipefactory@gmail.com በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ በኢ- ሜይል በማግኘት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

4.     ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለተወዳደሩበት ሎት ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (..) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 500,000.00 አይበልጥም።

5.     ተጫራቾች የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና የጥሬ ዕቃዎችን ዝርዝር የቴከኒክ መስፈርት በአንድ ላይ የቴክኒክ የመጫረቻ ሠነድ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው በፖስታ በማሸግ እና ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው በፖስታ በማሸግ የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነድ (Financial Bid Offer) በማለት ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7.     በእያንዳንዱ ሎት ውስጥ ለተዘረዘሩት ጥሬ ዕቃዎች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።

8.     የውድድሩ አሸናፊ ተጫራቾች ጥሬ እቃዎችን የሚያቀርቡበትን ቀናት በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የማቅረቢያ ጊዜው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት።

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 830 ይከፈታል።

10. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

11. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29 / 09-18-70-18-26 መደወል ይችላሉ።

                      ባህር ዳር

 

አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ

Save Tender