በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፤- • አንድ ቦታ አገልግሎት መስጫ (መሶብ ) • የተለያዩ የቢሮ እቃዎች • የቢሮ መጋረጃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና ግዴታዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችለ መሆኑን እንገልፃለን።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፤-
- አንድ ቦታ አገልግሎት መስጫ (መሶብ )
- የተለያዩ የቢሮ እቃዎች
- የቢሮ መጋረጃዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና ግዴታዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችለ መሆኑን እንገልፃለን።
የተጫራቾች መስፈርት /ግዴታዎች
- ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያሥችል የምዝገባ ምስከር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግዢ ደንብ እና መመሪያ የሚያከብር::
- የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው። የ2017ዓ.ም ግብር ያልከፈሉ እና ለ 2018 ንግድ ፈቃዳቸውን ካላደሱ ከሆነ ከገ/ባ⁄ጽ⁄ ቤት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የመጨረሻዉን ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያወራረደበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለእያንዳንዳቸው 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል
- የጨረታው ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ከማ/ወ/ገ/ባ/ጽ/ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን ቤት መግዛት የሚችል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በ17/9/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰአት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። በማስታወቂያ የተነገረ የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰአት ገብቶ ካለቀ በኋላ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4፡30 ሰዓት በማ/ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የዉል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- አሸናፊው የተገዙ እቃዎችን ለማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ከፍል ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ እና የማይነበቡ ነገር ሊኖር አይገባም
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ በግልጽ ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ ፤ 0472260016/ 0472260145 ይደውሉ።
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
