አዲስ ሕይወት የጤና አገልግሎት ኃላ.የተ. የግል ማህበር (አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል) አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የበረንዳና መስኮት ግሪሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የእንጨት በሮች፤ የዩፒኤስ ባትሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን በ4 ምድብ መድቦ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ሕይወት የጤና አገልግሎት ኃላ.የተ. የግል ማህበር (አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል) አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የበረንዳና መስኮት ግሪሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የእንጨት በሮች፣ የዩፒኤስ ባትሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን በ4 ምድብ መድቦ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ዝርዝር መግለጫ
እቃዎቹ የሚገኙበት ቦታ፡- አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ፣
ማሳሰቢያ፡-
1. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስገቡትን ዋጋ 25% ትክክለኛነቱ /በተረጋገጠ (CPO) በማስያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሰባት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እቃዎቹን መጥተው ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ሆስፒታሉ ድረስ በግንባር ቀርበው የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ ስባተኛ ፎቅ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታውን ያላሸነፈ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል። የጨረታው አሸናፊ በ 2 (ሁለት) ቀናት ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ እቃውን መውሰድ አለበት።
6. አሸናፊው ተጫራች በተወሰነው ጊዜ ሙሉ ክፍያውን ከፍሎ ንብርቶቹን ባያነሳ ያስያዘው ገንዘብ ለሆስፒታሉ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይስረዛል።
7. ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ በ7ኛ ቀነ- ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ቤት ቁጥር 088 አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል ከጌታሁን በሻህ ሕንፃ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
አዲስ ሕይወት የጤና አገልግሎት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር (አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል) ስልክ ቁጥር 7560፣ 0923280828 ወይም 0116180449 ይደውሉልን።
