ፀደይ ባንክ አ.ማ በብዛት 50 (ሃምሳ) የስልጠና ክፍል ወንበር ግዥ ለመፈፀም ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C)
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/0018/2017
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርቲፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸዉ ይገባል። ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሀምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሀምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አዲስ አበባ ለገሃር ስልክ ቁጥር 0115583187/0115581699
ፀደይ ባንክ አ.ማ
