Tender Detail

Tender Details


ፀደይ ባንክ አ.ማ በደቡብ ጎንደር እስቴ ከተማ የሚገኙ ከህንፃ ግንባታ የተረፉ የግንባታ ግብዓት እቃዎችን በጨረታ  አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


     ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C)

ከህንፃ ግንባታ የተረፉ የግንባታ ግብዓት እቃዎችን ለመሸጥ

              የጨረታ ማስታወቂያ

           የጨረታ ቁጥር 003/2018

ፀደይ ባንክ አ.ማ በደቡብ ጎንደር እስቴ ከተማ የሚገኙ ከህንፃ ግንባታ የተረፉ የግንባታ ግብዓት እቃዎችን በጨረታ  አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ግለሰብ /ድርጅት/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በጨረታው በሁሉም አይነት ወይም በከፊል መወዳደር ይቻላል ””
  2. የግንባታ ዕቃዎቹን በስራ ሰዓት ደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ከተማ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ቅ/ፅ/ቤት በመገኘት የጨረታ ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ ማየት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው የዋጋ ፎርማት ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል ፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል ፡፡ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ከበዛበትና ግልፀኝነት ከጐደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% በሲፒኦ/CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ 90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ  2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሁለት መቶ ብር /200.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
  8. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ፀደይ ባንክ አ.ማ

Save Tender