Tender Detail

Tender Details

  • Company ICMC General Hospital (አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል)
  • Address ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፀሀይ ሪል እስቴት ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 9 12 87 31 73
  • Websitehttps://www.icmc.com.et/
  • Deadline18 Jul 2026, 10:30 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-18 11:00:00
  • Categories Medical Equipment And Supplies , Health Care, Medical Industry Materials And Machinery

አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሕፃናት ድንገተኛ ክፍል (PEDI ER)፤ ለሕፃናት ታካሚ ክፍል (PEDI WARD) ለሕጻናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል (PEDI ICU) እና ለሕፃናት የተመላላሽ ታካሚ ክፍል (PEDI OPD) የሚያገለግሉ የሕክምና መገልገያ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: ICMC /Lo/ H/004/2018/2026

 

አይ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሕፃናት ድንገተኛ ክፍል (PEDI ER) ለሕፃናት ታካሚ ክፍል (PEDI WARD) ለሕጻናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል (PEDI ICU) እና ለሕፃናት የተመላላሽ ታካሚ ክፍል (PEDI OPD) የሚያገለግሉ የሕክምና መገልገያ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

የተጫራቾች መወዳደሪያ መስፈርቶች እና መመሪያዎች፡

1.     ሕጋዊ ሰነዶች፡ በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.     የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ተጫራቾች በሚያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ ከቫት (VAT) በፊት 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በድርጅቱ ስም ከተረጋገጠ ባንክ የሚከፈል የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

·        የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ እና ተጨማሪ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናትን የሚሸፍን ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡

3.     የሰነድ አቀራረብ፡ ተጫራቾች የቴክኒካል (Technical) እና የፋይናንሺያል (Financial) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

4.     የጨረታ ሰነድ ግዢ፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አምስተኛ ፎቅ በሚገኘው የፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ፣ ለማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአንዱ ሎት በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ:

·        ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓ ይዘጋል::

·        በዚሁ ዕለት ከቀኑ 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3 ፎቅ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

·        የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

6.     የጨረታው ፀና የሚቆይበት ጊዜ፡ ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) የሥራ ቀናት ስለሆነ፣ ተጫራቾች ይህንን አውቀው መቀበላቸውን በኦሪጅናል የቴክኒካል ነዳቸው ላይ ማረጋገጥ (መግለጽ) አለባቸው።

7.     የድርጅቱ መብት፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፤ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፀሀይ ሪል እስቴት ጀርባ

ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥራችን +2519 12 87 31 73 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል

Save Tender