Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Nominees
  • Address , Phone: 011-156 99 92
  • Website
  • Deadline21 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-07-21 10:30:00
  • Categories Billboards And Digital Advertising

የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር Computers Anti-Virus  እና Digital Light Box ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል፡፡


ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

     Commercial Nominees PLC

  የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/38/2018

 

የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር Computers Anti-Virus  እና Digital Light Box ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል፡፡ በዚህም

ሎት1፡- Computers Anti-Virus

ሎት2፡- Digital Light Box ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10፡30) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ

ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-1-569992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

Save Tender