በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር በስሩ ለሚገኙት አቡነ ጴጥሮስ ትምህርት ቤቶች በሎት 1 እና በሎት 2 በተገለጹት ዘርፎች ላይ ግዢ ለመፈፀም እና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ቁጥር 001/2019
የግንባታና ስራ እና የፈርኒቸር ግዢና ጥገና ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር በስሩ ለሚገኙት አቡነ ጴጥሮስ ትምህርት ቤቶች በሎት 1 እና በሎት 2 በተገለጹት ዘርፎች ላይ ግዢ ለመፈፀም እና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ሎት1. በት/ቤቶቹ ግቢ ውስጥ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታና የፓርቲሺን ስራ ማሰራት ሎት2. ለት/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ብዛት ያላቸው ፈርኒቸሮች (ዴስክ ወንበር፣ ጠረጴዛ ወዘተ) ግዢ እና የሚጠገኑ የፈርኒቸር እቃዎችን
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
3. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ስር በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ለግንባታና ፓርቲሽን ስራው የስራ ተቋራጭነት የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
6. ከላይ የተዘረዘሩትን ዶክመንቶች ኮፒ አድርጎ በማቅረብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ገቢ ማድረግ የሚችሉ፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በደረሰኝ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ያለ ስርዝ ድልዝ በግልጽ በመጻፍ አስከ አስረኛው ቀን 10፡00 ስዓት ዋና እና ኮፒ በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተሞላው ዋጋ ለ60 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
9. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO)፣ ቢድ ቦንድ(BD Bond) ወይም በቼክ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም አሸናፊ ድርጅቶች ውል በሚገቡ ሰዓት 10 ፐርሰነት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተቋሙ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ- አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ህንጻ ጎን KCBC ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር B1-606/1
ለበለጠ መረጃ 0985953949/0987972785 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር
