Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Police College (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ)
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0942410695
  • Websitehttps://oromiapolicecollege.edu.et
  • Deadline22 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-07-22 10:30:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

የኦሮሚያ ፖሊስ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ አባሎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ የአትክልት ሾርባ ባለ 240 ግራም፣ የስጋ እስቃጥላ ባለ 240ግራም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል።


በኦሮሚያ ፖሊስ የተዘጋጀ አስቸኳይ

ግ/ጨ/01/29 የበጀት ዓመት

የኦሮሚያ ፖሊስ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ አባሎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ የአትክልት ሾርባ ባለ 240 ግራም፣ የስጋ እስቃጥላ ባለ 240ግራም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡- ሎት አንድ፡-

ደረቅ ሬሽን ኮቾሮ

ሎት ሁለት:-

1. የአትክልት ሾርባ ባለ 240ግራም

2. የስጋ እስቃጥላ ባለ 240ግራም

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።

1.    ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2.    የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3.    በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4.    ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚወዳደርበት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

5.    ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።

6.    ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስይዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7.    የጨረታ ስነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8.    አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ የማጓጓዣ፣ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

9.    ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ እና ሲያስገባ የየሎቱን ሰነድ ለየብቻ ማቅረብ አለበት። የተለያዩ ሎት በአንድ ሰነድ በማዘጋጀት ወደ ሳጥን የሚያስገባ ድርጅት (ተወዳዳሪ) ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

10.        ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ቫት እና ማንኛውንም ወጪን ጨምሮ መሙላት አለበት። ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበ ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።

11.        ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 15/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።

12.        ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 15/11/2018 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ግዥ አገልግሎት መምሪያ ውስጥ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

13.        ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ፡-

አድራሻ፡-ኦሮሚያ ፖሊስ አ/አበባ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አካባቢ

ለተጨማሪ መረጃ፡-09 13 10 89 90 ወይም 09 96 05 47 78 መደወል ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ፖሊስ

Save Tender