Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 681 17 92
  • Website
  • Deadline23 Jul 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-07-23 15:00:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ፣ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ እህል ፣ ሸቀጣ ሸቀጥ፣ በርበሬ፣ ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት አቅርቦት ለስድስት ወር ማለትም ከነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን።

1.    በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/Tin Number/ ማስረጃ የአላቸውና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በጥሬ ገንዘብ ፡ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያሲዙ መሆኑን

2.    የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3.    ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር / መ/ቤቱ የአዘጋጀዉን የጫረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።

4.    ተጫራቾች ህጋዊ የምግብ አህል, ሸቀጣ ሸቀጥ, በርበሬ, ቅመማ ቅመም እና የማገዶ እንጨት ለእያንዳንዱ የንግድ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ የአላቸው።

5.    ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።

6.    ማንኛዉም ተጫራች ፖስታዉን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመምሪያዉ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጫረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ02/10/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 16/11/2018 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ መሆኑንና ጨረታው በዚሁ እለት በ 16/11/2018 ዓ/ምከቀኑ 8፡30 ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.    አሸናፊዉ በየወሩ እንደ ህግታራሚዎች ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምር ሊቀንስ የሚችል ሲሆን እንዲቀርብ መምሪያዉ በሚገልፀዉ መጠን በየወሩ የሚቀርብ መሆኑን እና አሽናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

8.    የዉድድሩ ሁኔታ በተናጥል በየዘርፉ በነጠላ የሚወዳደሩ መሆኑን እና ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት

9.    ለበለጠ መረጃ ካስፈለገዎት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 011 681 1792 መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

10.        መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን።

 

የሰ/ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

Save Tender