የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሎት 01 በዳዬ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ፥ ሎት 02 በዳዬ ከተማ አስተዳደር ሰቴድየም ቀበሌ እና ሎት 03 በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፈለ ከተማ የወጣት ሴቶችና ልጃገረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያገለግል የሼድ ስራ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የማምረቻ እና የመሸጫ ሼድ ሥራ
የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሎት 01 በዳዬ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ፥ ሎት 02 በዳዬ ከተማ አስተዳደር ሰቴድየም ቀበሌ እና ሎት 03 በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፈለ ከተማ የወጣት ሴቶችና ልጃገረዶችን ኑሮ ለማሻሻል የሚያገለግል የሼድ ስራ በተዘጋጀው ዲዛይን መሠረት ጥቃቅን እና አነስተኛ በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ብቻ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት መካከል ጨረታውን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
- በብረታ ብረት እና እንጨት ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ማህበራት፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ የሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ቢሮ (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) በመቅረብ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሀምሌ 20, 2018 (July 27, 2026) ተከታታይ የሥራ ቀናትና ሠዓት በመጠቀም (መወዳደር በፈለጉት በአንዱ ሎት ብቻ) ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር / በመክፈል መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል፡አንድ ኦሪጂናልና አንድ ኮፒ ቲክኒካል በአጠቃላይ በአንድ ትልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ እና በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስክ ሀምሌ 20, 2018 (July 27, 2026) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በሥራ ቀንና ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ30 ሠዓት በሄልቬታስ-አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት (ሀዋሳ ፒያሳ በሚኘው ንብ ህንፃ ስምንተኛ ፎቅ) ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0939064059/0911331955
የሄልቬታስ–አፕ ውሜን ሀዋሳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
ሀዋሳ
