Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁ
የተበዳሪው/     የመያዣ ሰጪው   ስም
የንብረት/ፕሮጀክት አድራሻ
የንብረት/ፕሮጀክት ዝርዝር
የቦታ ስፋት
የጨረታ መነሻ ዋጋ (በብር)
የጨረታ ሁኔታ
የጨረታ ደረጃ
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1
ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ
የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ(በትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኤልክትሪክ ሥራዎች እና የክምች ዕቃዎች
6.83

ሄክታር

ብር 457,236,714.80 (አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ  ሰባት መቶ አስራ አራት ብር ከሰማንያ ሳንቲም)
ዝግ
አንደኛ
ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም               ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት
2
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 08
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤የህንፃ ግንባታዎች፤ የኤሌክትሪክ ሥራዎች፤ ማሽነሪዎች፤ ቁሳቁሶች፤ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፤ የጥረ ዕቃና የምርት ክምችት
1,678 ካ.ሬ ሜትር
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
ልዩ ድርድር
ሁለተኛ
ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት

ማሳሰቢያ፤

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 11 እና ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ እንደየቅደምተከተላቸው ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
  3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከቱት ቀናት 4፡00 ሰዓት ላይ ተከፍቶ እስከ 6፡00 ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፡፡ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወከሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፡፡
  6. አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ የባንኩን የብድር መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ከፊል ብድር ሊመቻችለት ይችላል (ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ብቻ) ፡፡
  8. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል፡፡
  9. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎበኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቱን መጎበኘት ይችላሉ፡፡
  10. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011–524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

Save Tender