Tender Detail

Tender Details

  • Company በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
  • Address ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 ፡ አማራ ክልል፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0914711156
  • Website
  • Deadline02 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-08-02 10:30:00
  • Categories Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኘው መድኃኒት ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2019

 

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኘው መድኃኒት ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

1.    ተጫራቾች - የዘመኑን ግብር የከፈሉ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን/፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት የብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክክለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች አንተርፕራይዝ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ።

4.    ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጭ (መዝጋቢ አካል) የተሰጠ ህጋዊ የውክልና ማስርጃ ማቅረብ ይኖርበታል።

5.    ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማኅተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎከ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ /ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው።

6.    ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከጠዋቱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል። ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

7.    ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል።

8.    ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉትን ዕቃ የኢንተርፕራይዙ ንብረት ከፍል የሚገኝበት ቦታ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

9.    ተጫራቾች አሽናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት CPO ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

10.        አሽናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ህጐች ማከበር አለባቸው።

11.        ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0921269119 መጠቀም ይችላሉ።

 

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርኘራይዝ

Save Tender