የስልጤ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የዞኑን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል ፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የዞኑን ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ በመስኩ
በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርተፍኬት
የአመቱ በመንገድም ይሁን ግቢ ውስጥ ለሚደርስ አደጋ (ለሕይወትና ለንብረት)የታደሰ የሙሉ ኢንሹረንስ ውል ማቅረብ የሚችል ፡።
ተጫራቹ ከሚመለከተው አካል አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ::
የገራጅ ቤቱ ስፋት ከ2000 ካሬ ያላነስ ሆኖ የግል ከሆነ የካርታ ኮፒ የኪራይ ከሆነ የአንድ አመት የክራይ ውል ማቅረብ የሚችል ፡፡
በአዲሱ የፌዴራል ትራንስፖርት ሚኒስቴር የደረጃ አሰጣጥ መሰረት ደረጃ አራት ወይም ከዚያ በላይ ያለው ሆኖ ለደረጃው የተሰጠውን ቴከኒካል መስፈርት ማሟላት ሚችል፡፡
ለደረጃው የሚያስፈልጉት ሰራተኞችን ለሶስት ወር በተከታታይ ደመወዝ የተከፈለበትን ፔሮል፣የኮንትራት ሰራተኞች ካሉ ውል እንዲሁም በመስፈርቱ መሰረት የሁሉንም የትምርት ዶክመንት ማያያዝ ሚችል እና ሰራተኞችን የስራ ግብር ለገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የብር 80,000.00/ሰማኒያ ሺህ ብር/ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንት ማያያዝ የሚችል
ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመከፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ግልጽ በሆነ ጽሁፍ በመሙላት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዱን አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲዘመን ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ፡ የጨረታ ሳጥኑ በ10 ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰአት ይከፈታል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ስበለጠ መረጃ 0467710586/0010/0511 መደወል ይችላሉ
በማዕከላዊ ኢ/ክ/መ ስልጤ ዞን ፋይ/መምሪያ
