ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ የድርጅቱን መዋቅር ፤ የስራ ምዘና ፤ የደሞዝ ስኬል እና አጠቃላይ የጥቅማ ጥቅም ማእቀፍ የሚያጠና ልምድ ያለው አማካሪ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ፡፡
የመዋቅር፤ የስራ ምዘና፤ የደሞዝ ስኬል፤ እና አጠቃላይ ጥቅማ ጥቅም አጥኚ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ የድርጅቱን መዋቅር ፤ የስራ ምዘና ፤ የደሞዝ ስኬል እና አጠቃላይ የጥቅማ ጥቅም ማእቀፍ የሚያጠና ልምድ ያለው አማካሪ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ፡፡
ስለሆነም ፡
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲሁም የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ፕላዛ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 400.00(አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን በመለየት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በፖስታ ውስጥ በማድረግ ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት በተ.ቁ 02 በተገለጸው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡15 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6 ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 03 87/0909633424
ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
