ኬር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ኬር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪዎቹ በሚገኙበት አድራሻ በአዳማ ኬር ኢትዮጵያ ወደ ሶደሬ መንገድ ጥቁር አባይ ሆቴል ፊትለፊት ባለው TAF ማደያ አለፍ ብሎ በሚያስገባው የኮብል ስቶን ንጣፍ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ ባለው የመጋዘን ቢሮ ውስጥ እና በደብረታቦር ኬር ቢሮ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰአት ድረስ መመልከት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፓስታ/ በአዲስ አበባ ብስራተ ገብራኤል ከጋና ኤንባሲ ወይም ከክሩዝ ት/ቤት ጎን በሚገኘው ኬር ኢትዮጵያ መስሪያቤት እንግዳ መቀበያ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአፍሮ ቴንደር፡ 2መርካቶ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ ተሽከርካሪዎችን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር ዓይነትና ብዛት፣የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር በኬር ኢትዮጵያ አካውንት ቁጥር 1000000958976 አምስት መቶ ብር ብቻ /500/ እየከፈሉ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በመያዝ በአፍሮ ቴንደር፡ 2መርካቶ እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳር እንዲሁም በአዳማ ኬር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ መዝጊያ ቀን ነሃሴ 15 ፣ 2018 ዓ. ም ከቀኑ 6፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ብስራተ ገብራኤል ከጋና ኤንባሲ ወይም ከክሩዝ ት/ቤት ጎን በሚገኘው ኬር ኢትዮጵያ መስሪያቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0116183294፣ 0923084216 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ኬር ኢትዮጵያ
