Tender Detail

Tender Details

  • Company ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION
  • Address , Phone: 011-5512400
  • Website
  • Deadline20 Aug 2026, 2:23 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document Price
  • opening date2026-08-05 14:23:00
  • Categories Food And Beverage , Food Items And Drinks

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ማህበር በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለስፖርተኞች የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ማህበር በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለስፖርተኞች የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ፤
  2. የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO) ሰርተፍኬት ያለው፤
  3. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መስቀል አደባባይ በሚገኘው በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰሜን ምዕራብ ዲስትሪክት አንበሳ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4B ስፖርት ጽ/ቤቱ በመውሰድ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10(አሥር) የሥራ ቀናት ውስጥ መጥተው ሰነዱን በመግዛት ሞልተው ሊያስገቡ ይችላሉ፤
  4. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ (Specification) በሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከሰኞ እስከ ዓርብ ከቀኑ 9፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ 9፡15 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በስፖርት ማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፤
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 300,000.00(ሦስት መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ(CPO) ማስያዝ አለባቸው፤
  6. ተጫሮቾች አስፈላጊ ህጋዊ ሰነዶች እና የሚጠየቁ ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ መግለጫ በተለያዩ ፖስታዎች በማሰግና በአንድ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  7. ተጫሮቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙት ሲ.ፒ.ኦ(CPO) አሸናፊው ተለይቶ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
  8. ስፖርት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  9. የስፖርት ማህበሩ የስራ ሠዓት፡-

ከሰኞ እስከ ሐሙስ          ከ2፡00 – 6፡00

ከሠዓት በኋላ    ከ7፡00 – 10፡00

ዓርብ ጥዋት     ከ2፡00 – 5፡30

ከሠዓት በኋላ    ከ7፡30 – 11፡00

ለበለጠ መረጃ በሚከተለው አድራሻ መጠቀም ይችላሉ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስፖርት ማህበር

ስልክ ቁጥር ፡- 011-5-15-96-26

አዲስ አበባ

Save Tender