የዶሮ መኖ ጥሬ ግብዓት ግዥ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በመራባት ላይ ላሉ ዶሮ መኖነት የሚውል የጥሬ ግብዓት ጥራቱን የጠበቀ ምርት ማለትም፡-
- ፉርሽካ
- አኩሪ አተር ፋጉሎ
- የኑግ ፋጉሎ
- ልዮር ቫይታሚን ፕሪሚከስ 0.25% ወይም 0.5%
- እስታርተር ቫይታሚን ፕሪሚክስ 0.25% ወይም 0.5%
- ሚትዮኒን
- ላዮሲን
- የተፈጨ ሥጋና አጥንት
- አንደኛ ደረጃ በቆሎ
በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች
- ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው እና ማዕከሉ በምፈልገው መጠን እና ጥራት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የጨረታ እሴት ታከሰ ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው፣ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው እና ካሁን ቀደም በተመሳሳይ ሥራ የተሻለ አፈፃፅም ያለው፤ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና ኦሪጂናል በማቅረብ አመሳከሮ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የተሟላ ሠነድ ለየብቻ /አንድ/ኢሪጂናል 2 ሁለት/ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በአሪጂናል 150,000/ አንድ መቶ ሃምሳ ሺ ብር /C P O/ የተያዘበት ሠነድ ገብቶ መታሽግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግሥት ቦንጋ ዶሮ ዕርባታ በኩል የማይመለሰ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፍል ከቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል በኩል ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የመዝጊያና መከፈቻ ቀን ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኝት የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማንኛውም ኦሪጂናል መረጃ ፊረማና ማህተም ሊኖረው ይገባል፡፡
- የጨረታው አሽናፊ በ7 ቀናት ውስጥ ውል ገብቶ ሥራውን መጀመር ይኖርበታል። 3ኛ ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበስጠ መረጃ፡- 0934449883/0910409901 ላይ ደውለው ይጠይቁ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቦንጋ ዶሮ ዕርባታ ማዕከል
✨ messages.ai_summary
- Procurement: Raw materials for chicken feed, including soybean, fava bean, noug bean, layer and starter vitamin premixes (0.25%/0.5%), methionine, lysine, meat and bone meal, and first-grade maize.
- Issuer: Bonga Chicken Breeding Center, South West Ethiopia Peoples Region.
- Key dates: Bids close on the 15th day and open on the 16th day after newspaper publication at 11:30 and 4:30, respectively.
- Costs/guarantee: Bid document price ETB 500; bid bond ETB 150,000 (CPO). Winner must provide a 10% contract performance guarantee.
- Eligibility: Must have a renewed business license, TIN, current tax payment, VAT/registration certificates, and prior experience in similar works.
