የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ ሙሉና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች ፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ፣ የተሸከርካሪ መብራቶች እና ፊልትሮዎች ፣ አሮጌ ጠረጴዛ ፣ ወንበር እና ሼልፍ ፣ የተለያዩ ካርትሬጅ ፣ ባዶ ላርጐ ጀሪካን በለ 5 ሊትር ፣ የቀለም ቆርቆሮዎች ፣ የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጐማዎች ፣የተለያዩ ጋዜጣዎች ፣ የተቃጠለ ዘይት ፣ ፈርነስ ፣ ያገለገሉ የIT እቃዎች (ኮምፒውተር ፣ ላፕቶፕ ፣ ዩፒኤስ ፣ ፕሪንተር) እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች:–
- ያገለገሉ እቃዎች ያሉበትን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጨረታ መዝጊያው ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀዉ መሠረት ይሆናል፡፡
- ለአገለገሉ እቃዎች ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያው ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው ነሀሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአጭር የስልክ ቁጥር በ8868/0114163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!